የስደተኞች የቤተሰብ ማመልከቻ ቤተሰቦችን ስለማገናኘት
ዘመዶቻቸው ከሃገር ውጭ የሚኖሩ ብዙ የዩናይትድ ስቴትስ ነዋሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር በአንድ ላይ መኖር ይፈልጋሉ፡፡ ስደተኞችን በተመለከተ ኮልማን ጃክሰን የግል ኩባንያ ተጋቢዎችን፣ ወንድማማቾችንና እህትማማቾችን፣ ወላጆችን እና ሌላ የቅርብ ዘመዶችን በቤተሰብ የስደተኞች ማመልከቻ አንድ ላይ መኖር እንዲችሉ በማድረግ ያግዛል፡፡ በዳላስ ቴክሳስ በሚገኘው የህግ ክፍላችን ልምድን ባካበቱ የህግ ባለሙያዎቻችንና ሰራተኞች አጠቃላይ፣ ሚስጥራዊ እና ጥንቃቄ የተሞላበት መንገዶችን በመከተል፣ የአመልካች ቤተሰቦችን ሁኔታ በመረዳት፣ ያሉትን አማራጮችንና እድሎች በዝርዝር በመመልከት ጠቃሚ የሆኑ ምክሮችን በመስጠት እና ጉዳዩን በመከታተል የያዙት አላማ ከግብ እንዲደርስ ያደርጋል፡፡