የስደተኞች የቤተሰብ ማመልከቻ ቤተሰቦችን ስለማገናኘት

ዘመዶቻቸው ከሃገር ውጭ የሚኖሩ ብዙ የዩናይትድ ስቴትስ ነዋሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር በአንድ ላይ መኖር ይፈልጋሉ፡፡ ስደተኞችን በተመለከተ ኮልማን ጃክሰን የግል ኩባንያ ተጋቢዎችን፣ ወንድማማቾችንና እህትማማቾችን፣ ወላጆችን እና ሌላ የቅርብ ዘመዶችን በቤተሰብ የስደተኞች ማመልከቻ አንድ ላይ መኖር እንዲችሉ በማድረግ ያግዛል፡፡ በዳላስ ቴክሳስ በሚገኘው የህግ ክፍላችን ልምድን ባካበቱ የህግ ባለሙያዎቻችንና ሰራተኞች አጠቃላይ፣ ሚስጥራዊ እና ጥንቃቄ የተሞላበት መንገዶችን በመከተል፣ የአመልካች ቤተሰቦችን ሁኔታ በመረዳት፣ ያሉትን አማራጮችንና  እድሎች በዝርዝር በመመልከት ጠቃሚ የሆኑ ምክሮችን በመስጠት እና ጉዳዩን በመከታተል የያዙት አላማ ከግብ እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

በቅርብ ዘመድ እና በአማራጭ የዘመድ ማመልከቻ እገዛ ስለማድረግ

የቤተሰብ የስደተኝነት ማመልከቻ በቅርብ ዘመድ ማመልከቻ ወይም በአማራጭ የዘመድ ማመልከቻ ሊቀርብ ይችላል፡፡

የቅርብ ዘመድ ማመልከቻ

በቅርብ ዘመድ ማመልከቻ ለማመልከት አመልካች የዩ.ኤስ. ዜግነት ያለው /ያላት  ባለቤት ከሆነ/ች፣ የዩ.ኤስ. ዜግነት ያለው /ያላት ልጅ ወይም የዩ.ኤስ. ዜግነት ያለው /ያላት ልጅ ወላጅ ከሆነ/ች፣ የዩ.ኤስ. ዜግነት ያለው /ያላት ሰው/ሴትዮ ቢያንስ 21 አመት የሞላው/ት ከሆነች በቅርብ ዘመድ ማመልከቻ ለማመልከት ብቁ ይሆናሉ፡፡ በስደተኞች ህግ መሰረት ልጅ ማለት ያላገባ/ች እና ማመልከቻው በተሞላበት ጊዜ ከ 21 አመት በታች የሆነ/ች ማለት ነው፡፡ በቅርብ ዘመድ ማመልከቻ ቪዛ ወዲያውኑ ማግኘት ይቻላል ነገር ግን የማመልከቻው ሂደት ብዙ ወራትን ሊወስድ ይችላል፡፡

ሌላ አማራጭ የዘመድ ማመልከቻ

ለቅርብ ዘመድ ማመልከቻ ወይም በእጮኝነት ለማመልከት ብቁ ያልሆኑ የቤተሰብ አባላት በ U.S. ስቴት ዲፓርትመንት በተቀመጠው ሌላ የአማራጭ የዘመድ ማመልከቻ ማመልከት ይችላሉ፡፡ አንዳንድ የግሪን ካርድ ያላቸው ሰዎች ዘመዶችም በሌላ አማራጭ የዘመድ ማመልከቻ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ በፍቅረኛዎ ስም በሌላ አማራጭ የዘመድ ማመልከቻ የሚጠይቁ ከሆነ የእርስዎ ዘመድ የቪዛ ቁጥር እስከሚገኝ ድረስ ሊጠብቁ ይችላሉ፡፡ እንደ ቅደም ተከተሉ ቪዛው ከመድረሱ በፊት አመታትን ሊወስድ ይችላል፡፡ በመጨረሻም ባለቤትና ህፃናቶች እንደተጠቃሚነታቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል፡፡

ለስደተኝነት አስፈላጊ የሆኑ ህግ ነክ ማብራሪያዎች

ስደትን በተመለከተ መረጃዎችን ሲፈልጉ ወደ ህግ ክፍላችን በመምጣት ያግኙን፡፡ ስለ ራስዎ እና ስለ ቤተሰብዎ ዝርዝር መረጃዎችን በመጠየቅና የተገኙትንም መረጃዎችን በመተንተን የእርስዎን የግል ሁኔታንና ህግን መሰረት ያደረገ ተገቢ የሆነ ማመልከቻ እናዘጋጃለን፡፡ በቅርብ ዘመድ ማመልከቻ ወይም በሌላ አማራጭ የዘመድ ማመልከቻ ለማመልከት ለእርሰዎ ተመራጭ ካልሆነ በሌሎች አማራጮች የስደተኝነት ጥያቄ በባለቤት ወይም  በአስጠጊ በተፈፀመ ወንጀል ወይም የቤት ውስጥ ጥቃትን ጨምሮ በእነዚህ ሁኔታዎች ላይ ልንረዳዎት እንችላለን፡፡

 

214-599-0431 ቀጠሮ ለማስያዝ በመደወል ወይም በዌብሳይት በቀጥታ ያግኙን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *